Nicotto Town



わかっちゃいるけど その106

giugno 6 martedi ☀︎ 31/15℃

13331歩
ጎንደር,Gondar ethiopia

ጎንደር ከ1628 ዓ ም ጀምሮ ለ200 ዓመታት የአፄወች መናገሻ በመሆኗ የምትታወቅ የዓለም ታዋቂ የታሪክ ተመራማሪወችን የምትስብ ውብ ከተማ ናት።

የዘመኑ አፄዎች የገነቧቸው ቤተ መንግስቶችና አብያተ ክርስቲያናት  (ፋሲል ግንብ፣ የጉዝራ፣ ጎመንጌ- አዘዞ ገነተ እየሱስ፣ ጎርጎራ ማንዴ ወዘተ) የከተማዋንና የኢትዮጵያን ታሪክ ለዓለም ጥሩ ገፅታ ለመሆናቸው ከተለያዩ  ክፍለዓለማት እንደ ጎርፍ ለጉብኝትና ታሪክን ለመቃኘት የሚተመውን ለአብነት መጥቀሳችን ሁላችንም ያስማማናል።

ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ከወረረ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአርበኝነት በረሀ ሲወርድ ያኔ ነበር የጣሊያን ወራሪው ሀይል ሕዝብን በማፈናቀል መሬትን መንጠቅ የጀመረው (see picture of Italian General addressing his army on top of Fasil Castle) ።

ለአብነት የጎንደር ሲኒማ ቤት በፋሽስት ጣሊያን ከመሰራቱ በፊት እርስትነቱ የአቶ መንክር ተገኘ የተሰኙ በዚያን ዘመን ጎንደር ከተማ ውስጥ በጣም የላቁና የመጠቁ ነገረ ፈጅ ወይንም ጠበቃ ነበሩ።

በዚያን ዘመን የህግ ባለሙያ ወይንም ጠበቃ ነበር ወይ ለምትሉ?  በሀገራችን በዘመናዊ ትምህርት ቤት ባይማሩም ከቤተክህነት ትምህርትን የቀሰሙና ጥሩ አንደበተ ርህቱ የሆኑ ሰወች በጠበቃነት ተሰማርተው ይሰሩ ነበር።

ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ቀደምት ጥንታዊ  ግሪካዊያንም በድሮ ዘመን የአቴንስ ጸሐፊዎችና ጥሩ  ተናጋሪወች በጠበቃነት ያገለግሉ እንደነበር የታሪክ  ድርሳናት ያመለክታሉ ።




月別アーカイブ

2025

2024

2023

2022

2021

2020

2019

2018

2017

2016

2015


Copyright © 2025 SMILE-LAB Co., Ltd. All Rights Reserved.